የግብርና ሚኒስትሩ ከዓለም ባንክ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 21 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ከዓለም ባንክ የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ
በዚህ ወቅት በኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ ከሚሰሩ ስራዎች ጋር በተያያዘ ከዓለም ባንክ የስራ ኃላፊዎች ጋር በቅንጅት እየሰሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡
በአየር ንብረት ለውጥ፣ በምግብ እና የምግብ ደህንነት፣ በአፈር ጤንነትና በውሃ ሃብት አያያዝና አጠቃቀም፣ በግሉ ዘርፍ የኢንቨስትመንት ስራዎች ላይ መምከራቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በተጨማሪም የገጠር የፋይናንስ አቅርቦት እና አገልግሎትን ወደ አርሶና አርብቶ አደሩ ማህበረሰብ ተደራሽ የማድረግ ስራዎች ላይ በስፋት እና በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ በግብርናው ዘርፍ ላይ የሚሰሩ ፕሮጀክትና ፕሮግራሞች ላይ በሚሰሩት ስራ ላይ ተወያይተዋል፡፡