Fana: At a Speed of Life!

ቼልሲ ማውሪሲዮ ፖቼቲኖን አዲሱ የክለቡ አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 21 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ማውሪሲዮ ፖቼቲኖን አዲሱ የክለቡ አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙን አስታውቋል፡፡

የቀድሞው የቶተንሃም እና የፓሪስ ሴንት ዠርሜን አሰልጣኝ ፖቼቲኖ ክለቡን በዋና አሰልጣኝነት ለመያዝ ሲነጋገሩ መቆየታቸው ይታወሳል።

ሜትሮ ስፖርት እንዳስነበበው የ51 ዓመቱ አሰልጣኝ ቼልሲን በዋና አሰልጣኝነት ለመምራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

ከስምምነቱ በኋላ ፖቼቲኖ ቼልሲ በከፍተኛ ገንዘብ ወደ ክለቡ ባስፈረማቸው ተጫዋቾች ላይ ትኩረታቸውን እንደሚደርጉ እና ለአካዳሚ ወጣቶችም እድል እንደሚሰጡ ገልፀዋል፡፡

እየታየ በሚታደስ ተጨማሪ አንድ አመትን ባካተተ በሁለት ዓመት ኮንትራት ክለቡን ለማሰልጠን የተስማሙት አርጀንቲናዊው አሰልጣኝ በመጪው የውድድር ዓመት የምዕራብ ለንደኑን ክለብ ወደ ተፎካካሪነት ይመልሱታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በውጤት ማጣት ቀውስ ውስጥ የውድድር አመቱን የጨረሰው ቼልሲ በሊጉ 12ኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቁ የሚታወስ ነው፡፡

ፖቼቲኖ ለቼልሲ በአምስት አመታት ውስጥ ስድስተኛው ቋሚ አሰልጣኝ ሲሆኑ፥ ክለቡ በአዲሱ ባለቤት ቶድ ቦህሊ ባለቤትነት ከተያዘ በኋላ ደግሞ አራተኛው አሰልጣኝ ሆነው ክለቡን ይረከባሉ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.