Fana: At a Speed of Life!

አውስትራሊያ ለአፍሪካ ቀንድ እና የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የ29 ሚሊየን ዶላር የሰብዓዊ ድጋፍ ይፋ አደረገች

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 21 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አውስትራሊያ ኢትዮጵያን ጨምሮ በድርቅ ለተጎዱ የአፍሪካ ቀንድ እና የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የ29 ሚሊየን ዶላር የሰብዓዊ ድጋፍ ይፋ ማድረጓን አስታውቃለች፡፡

በዛሬው እለት ይፋ የተደረገው ይህ የሰብዓዊ ድጋፍ የምግብ ዋስትና ቀውስ ላጋጠማቸው ዜጎች የሚውል መሆኑ ተገልጿል።

የአውስትራሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔኒ ዎንግ በሰጡት መግለጫ÷15 ሚሊየን ዶላሩ በኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ እና ኬንያ የሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሚውል መሆኑን ገልፀዋል፡፡

4 ሚሊየን ዶላሩ ደግሞ በየመን ለተከሰተው የምግብ እጥረት ድጋፍ ይውላል የተባለ ሲሆን ቀሪው 10 ሚሊየን ዶላር ደግሞ በየመን እና ዮርዳኖስ ለሚገኙ ስደተኞች የሚውል ነው፡፡

ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጀምሮ ለምግብ ዋስትና እጦት የተጋለጡ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ያነሱት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ፥ አሁን ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ 350 ሚሊየን ዜጎች ለምግብ ዋስትና ችግር ተጋላጭ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡

አውስትራሊያ በሱዳን በግጭት ለተጎዱ ዜጎች የ6 ሚሊየን ዶላር የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን አናዶሉ ኤጀንሲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.