ወልቂጤ ከነማ እና ኢትዮጵያ ቡና ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 21 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ26ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ወልቂጤ ከነማ እና ኢትዮጵያ ቡና ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡
ቀን 9 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ መድንን ያስተናገደው ወልቂጤ ከነማ 2 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል፡፡
የወልቂጤ የማሸነፊያ ጎሎችን በእለቱ ድንቅ ብቃቱን ያሳየው ጌታነህ ከበደ በፍፁም ቅጣት ምት እና በጨዋታ ማስቆጠር ችሏል፡፡
በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ሀድያ ሆሳዕናን የገጠመው ኢትዮጵያ ቡና 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል፡፡
አማኑኤል ዮሀንስ እና መስፍን ታፈሰ የኢትዮጵያ ቡና የድል ግቦች ያስቆጠሩ ሲሆን ባየ ገዛኸኝ የሃድያ ሆሳና ን ብቸኛ ጎል አስቆጥሯል፡፡
ውጤቱን ተክትሎ ቡናማዎቹ ደረጃቸውን ያሻሻሉ ሲሆን ነጥባቸውን 38 በማድረስ 5ኛ ደረጃ ላይ መቀመት ችለዋል፡፡