Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር ኤርጎጌ ከተመድ የሴቶች ልዑካን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 21 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢፌዴሪ የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተሥፋዬ ከተመድ የሴቶች ልዑካን ቡዳን ጋር ተወያይተዋል፡፡

ዶክተር ኤርጎጌ ÷ የተመድ የሴቶች በኢትዮጵያ ተወካይ የሆኑትን ሴሲሊ ማካሩባ በቢሯቸው አግኝተው ተወያይተዋል፡፡

በተጨማሪም ከእርሳቸው ጋር በተመድ የምሥራቅና ደቡብ ቀጣና ምክትል ዳይሬክተር የሆኑትን ዘቢብ ካቩማ ማነጋገራቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በውይይታቸው ዶክተር ኤርጎጌ  ÷ ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው ሴቶችና ሕፃናትን ለማብቃት እያከናወናቸው የሚገኙ ተግባራትን በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል፡፡

እንዲሁም የኢትዮጵያ መንግስት ሴቶችን በፖለቲካዊ ፣ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ለማብቃት ያለውን ቁርጠኝነት በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የተመድ ሴቶች በኢትዮጵያ ተወካይ የሆኑትን ሴሲሊ ማካሩባ ÷ የኢትዮጵያ መንግስት ሲያከናውን የቆያቸውን ተግባራት አድንቀዋል።

በውይይታቸውም የኢትዮጵያ መንግስት በሥርዓተ ጾታ እኩልነት እና የሴቶችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ላይ የሰራቸውን ሥራዎች ገልፀውላቸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.