Fana: At a Speed of Life!

የቻይና የህክምና ቡድን በዘውዲቱ መሸሻ ብርሃን ሕጻናት ማሳደጊያ ለሚገኙ ህጻናት ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና የህክምና ቡድን በዘውዲቱ መሸሻ ብርሃን የሕጻናት ማሳደጊያ ማዕከል ለሚገኙ ህጻናት ነጻ የጤና ምርመራ እና የህክምና አገልግሎት ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የህክምና ቡድኑ አገልግሎቱን የሚሰጠው በማዕከሉ ለሚገኙ 80 ህጻናት ሲሆን÷ ከህክምና በተጨማሪ የትምህርት እና የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡

የጤና ምርመራና ድጋፉ የተከናወነው የኢትዮጵያ ቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ከቻይና ቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ጋር በመተባበር መሆኑም ተገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዥዩዋን በዚህ ወቅ የህክምና ቡድኑ ለህጻናቱ ሙሉ ምርመራ የሚያደርግ መሆኑን ገልጸው÷ ህመም ለተገኘባቸውም ወዲያው የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ይደረጋል ነው ያሉት፡፡

በአገር ውስጥ የማይቻል ህመም የሚከሰት ከሆነም ወደ ውጭ ሀገር በበመውሰድ እንደሚያሳክሟቸው አረጋግጠዋል፡፡

አምባሳደሩ አክለውም÷ በቻይና እና ኢትዮጵያ መካከል ያለው ዘርፈ ብዙ ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል፡፡

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ በበኩላቸው÷ በዘውዲቱ መሸሻ ብርሃን የሕጻናት ማሳደጊያ ማዕከል አቅራቢያ የሚገኘው የጴጥሮስ ስቴሻላይዝድ ሆስፒታል ከህክምና ቡድኑ ጋር በጋራ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.