Fana: At a Speed of Life!

በሞስኮ ከተማ የድሮን ጥቃት መሰንዘሩ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሩሲያ ርዕሰ መዲና ሞስኮ ከተማ የድሮን ጥቃት መሰንዘሩን የከተማዋ ከንቲባ ሰርጌ ሶቢያኒን ተናገሩ፡፡

ዛሬ ማለዳ ድሮኖች በሩሲያ ዋና ከተማ ጥቃት በመፈፀም በሕንፃዎች ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን ነው ከንቲባው የተናገሩት።

ሶቢያኒን ነዋሪዎች ኢላማ ከተደረጉ ሁለት አፓርታማዎች እንዲወጡ ማዘዛቸው ተገልጿል።

ከንቲባው ከከተማው የህክምና አገልግሎት የተገኘን መረጃ በመጥቀስ በድሮን በተመታ ህንጻ ውስጥ ምንም አይነት ነዋሪ ላይ ከባድ ጉዳት እንዳልደረሰ ገልፀዋል።

በስፍራው ሁለት ሰዎች የህክምና እርዳታ መጠየቃቸውን ያነሱት ከንቲባው ወደ ሆስፒታል የተወሰደ ሰው እንደሌለ መግለፃቸውን አር ቲ ዘግቧል።

የሞስኮ ግዛት አስተዳዳሪ አንድሬ ቮሮቢዮቭ÷ ወደ ከተማዋ ጥቃት ለማድረስ ሲበሩ የነበሩ በርካታ ሰው አልባ አውሮፕላኖች በአየር መቃወሚያዎች ተመትተው መውደቃቸውን በቴሌግራም ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ አስታውቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.