Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል የአፈር ማዳበሪያ እጥረት እንዳጋጠመ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ በዘንድሮው የምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያ እጥረት እንደገጠመው አስታውቋል፡፡

ከመጋቢት 15 እስከ ግንቦት 15 ባለው ጊዜ ውስጥ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ ያለ መግባቱ ለተፈጠረው ከፍተኛ እጥረት በምክንያትነት ተነስቷል፡፡

የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አጀበ ስንሻው ÷ በዘንድሮው የምርት ዘመን ከአርሶ አደሩ የተሰበሰበ የአፈር ማዳበሪያ ፍላጎት 9 ነጥብ 2 ሚሊየን ኩንታል መሆኑን አንስተዋል፡፡

በክልሉ 5 ነጥብ 2 ሚሊየን ኩንታል ማዳበሪያ ለማቅረብ እንደታቀደ እና ይህ እቅድም ከአርሶ አደሩ ፍላጎት አንጻር 58 በመቶ ብቻ ማሳካት እንደሚያስችላቸው ነው የተናገሩት፡፡

እስካሁን ለአርሶ አደሩ 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ እንደቀረበ የገለጹት ኃላፊው 35 በመቶውን ማሳ መሸፈን እንዳስቻለም ገልጸዋል፡፡

በኤልያስ ሹምዬ

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.