በኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚ ጥሩ ውጤት እያስመዘገበ ነው – ምሁራን
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚ ጅምር እንቅስቃሴ ላይ የሚገኝ ቢሆንም ጥሩ ውጤት እያስመዘገበ እንደሚገኝ የምጣኔ ሀብት ምሁራን ገለጹ፡፡
በመዳወላቡ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህሩ አብይ ወርቁ (ዶ/ር) ፥ ዲጂታል ኢኮኖሚ ጊዜን፣ ገንዘብንና ወጪን ይቀንሳል ብለዋል።
ሥርዓቱ መጭበርበሮችን በማስቀረት ፍትሐዊነትን ለማረጋገጥ እንደሚያግዝም ነው የገለጹት።
በአርሲ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህር ሰዒድ አሊ በበኩላቸው ፥ ዲጂታል ኢኮኖሚ አገልግሎትን በማዘመን ያለንን ውስን ሃብት በአግባቡ እንዲተዳደር የሚያስችል መሆኑን አስረድተዋል።
በተጨማሪም በምርቶች ላይ ሰው ሰራሽ እጥረት እንዳይከሰት ቁጥጥር ለማድረግ ያስችላል ብለዋል፡፡
በዲጂታል ክፍያ ስርዓት ምን ያህል ንግድ እንደተፈጸመና የንግድ ስርዓቱን ለመቆጣጠር ያግዛል እንዲሁም የመንግስትም ገቢ እንዲያድግ ያደርጋል ነው ያሉት ምሁራኑ፡፡
በኢትዮጲያ ዲጂታል ኢኮኖሚን እውን ለማድረግ ኢንተርኔትን ተደራሽ ማድረግና የማህበረሰቡን ክህሎትና እውቀት ማሳደግ ትኩረት ሊሰጠው ይገባልም ብለዋል፡፡
በአልማዝ መኮንን