Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች ለማልማት ታቅዷል-የክልሉ ግብርና ቢሮ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል በ2015/16 የምርት ዘመን 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች ለማልማት መታቀዱን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

የ2015/16 ምርት ዘመን የመኸር ሥራዎች ንቅናቄ መድረክ በቡታጅራ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ ላይ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር እንዳሉት÷ በክልሉ በመኸር ወቅት ልማቱን ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው።

ከዚህም ከ951 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት የሚሆነው በአዝርዕት ሰብሎች፣ ቀሪው በቋሚ ተክሎች እንደሚለማ ገልጸዋል።

ዘንድሮ በአዝርዕት ለማልማት የታቀደው መሬት ካለፈው የምርት ዘመን ጋር ሲነፃጸር ከ200 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ብልጫ እንዳለው ጠቅሰዋል፡፡

ለዕቅዱ ስኬት ምርጥ ዘርና ማዳበሪያ ቀደም ብሎ መሰራጨቱን ጠቁመው÷ ከአፈር ማዳበሪያ ጋር በተያያዘ የሚስተዋለውን እጥረት ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በክልሉ በምርት ዘመኑ በሰብል ከሚለማው መሬት 97 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዷል መባሉንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.