ጣሊያን ለኢትዮጵያ የ7 ነጥብ 6 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አደረገች
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጣሊያን በኢትዮጵያ ለመልሶ ግንባታ ስራዎች የሚውል የ7 ነጥብ 6 ሚሊየን ዩሮ
ድጋፍ አድርጋለች፡፡
ድጋፉ በአፋር እና ደቡብ ክልሎች በጤና፣ ትምህርትና የንጹሕ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ላይ የሚሠሩ የመልሶ ግንባታሥራዎችን እና መሠረተ ልማቶችን ለማሻሻል እንደሚውል ተገልጿል፡፡
አምባሳደር አጎስቲኖ ÷የጣሊያን መንግስት በኢትዮጵያ ጉዳት የደረሰባቸውን የማኅበረሰብ ክፍሎች መደገፍ በመቻሉ እንደተደሰቱ መናገራቸውን በኢትዮጵያ የተመድ ፕሮጀክቶች ማስተባበሪያ ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡