Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከጎፈሬ የትጥቅ አምራች ድርጅት ጋር ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከጎፈሬ የትጥቅ አምራች ድርጀት ጋር  አዲስ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

በአዲሱ ውል መሰረት ሀገር በቀሉ የትጥቅ አምራች ተቋም ጎፈሬ ለቀጣይ አራት ወራት ለኢትዮጵያ ወንዶች እና ሴቶች እግር ኳስ ቡድኖች ለውድድር እና ለልምምድ የሚሆን የትጥቅ አቅርቦት ያደርጋል።

ጎፈሬ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ትጥቆችን ከሚያቀርቡ ድርጅቶች 50 በመቶ የዋጋ ቅናሽ የሚያደርግ ሲሆን ድርጅቱ ባለፉት ሁለት አመታት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የልምምድ መለያዎችን ሲያቀርብ መቆየቱ ይታወሳል።

የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ዋና ፀሐፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን፥ ብሄራዊ ቡድኑ ባለፉት  ዓመታት የጎፈሬ የትጥቅ ምርትን ሲጠቀም እንደነበር አንስተው በምርቶቹ ጥራት ደስተኛ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

የጎፈሬ  ትጥቅ አምራች ስራ-አስኪያጅ አቶ ሳሙኤል መኮንን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር የተደረገው የአጋርነት  ስምምነት በአፍሪካ ያለንን ገበያ ለማስፋት እየሰራን መሆኑን የሚያሳይ ነው ብለዋል።

በወርቅነህ ጋሻሁን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.