Fana: At a Speed of Life!

በፌዴራል ፖሊስ የሥራ እንቅስቃሴ ላይ የሚያጠነጥን “መለኞቹ” የተሰኘ ፊልም ተመረቀ 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዘጋቢ የድራማ ዘዉግ ስር የሚመደበዉ እና  የፌዴራል ፖሊስ ህዝብን በማገልገል ረገድ የሚሰራቸዉን ስራዎች መነሻ በማድረግ የተሰራው መለኞቹ የተሰኘ ፊልም ተመርቋል፡፡

የፊልሙ ፀሀፊ እና አዘጋጅ ታምሩ ብርሃኑ ÷ ፊልሙን ለማዘጋጀት ባለፉት አራት አመታት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ህዝብን በማገልገል ሂደት ዉስጥ  ያከናወናቸዉን ተግባራትና ያጋጠሙትን ፈታኝ ክስተቶች መነሻ በማድረግ የፊልም ታሪክ መረጣና የፊልም ፅሁፍ መዘጋጀቱን ተናግሯል።

በፊልሙ ላይ የተለያዩ ስመጥር እና ወጣት ተዋንያን እንዲሁም በፌዴራል ፖሊስ ዉስጥ በተለያየ የስራ ሀላፊነት ላይ የሚገኙ አባላትም  ተሳትፈውበታል ተብሏል።

በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈጉባኤ  አገኘሁ ተሻገር ፣ የቀድሞ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) ፣ የጦር ሀይሎች ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተገኝተዋል፡፡

በተጨማሪም የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ተመስገን ጥሩነህ ፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል እና ሌሎች ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ዲፕሎማቶች በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ታድመዋል፡፡

በፀጋዬ ወንድወሰን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.