Fana: At a Speed of Life!

የአዋሽ ወንዝ ሞልቶ የከፋ ጉዳት እንዳያስከትል የመከላከል ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በክረምቱ የአዋሽ ወንዝ ሞልቶ የከፋ ጉዳት እንዳያስከትል የተለያዩ የመከላከል ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኝ የወሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ  ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) ገለጹ፡፡

ሚኒስትሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷የአዋሽ ወንዝ በአፋር አና በኦሮሚ ክልሎች ጉዳት እንዳያሰከትል የቅድመ ማሰጠንቀቂያ ግንዛቤ ከመስጠት ጀምሮ የጎርፍ መገደቢያ ስራ ዎች ተከናውነዋል።

በሌሎቹ አካባቢዎች የጎርፍ አደጋዎችን ለመቀነስ በግድቦች የውሃ መውረጃ ቱቦዎች እየተሰሩ መሆናቸውን  ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡

የቅድመ መከላከል ስራዎችን ለመከላከል የሚያስችል የ258 ሚሊዮን ዶላር ከዓለም ባንክ መፈቀዱን የገለፁት ሚኒስትሩ ÷የአዋሽ ወንዝን ወደ መልካም እድል ለመቀየር ጥሩ አጋጣሚ ነው ብለዋል።

አዋሽ ወንዝ ከመጠን በላይ በመሙላት በየዓመቱ በአፋር እና በምስራቅ ኦሮሚያ ለበርካታ ሰወች ህይወት መጥፋት  እና ንብረት መውደም ምክንያት መሆኑ የሚታወሰ ነው።

በሲሳይ ጌትነት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.