Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይና ፕሬዚዳንት ትራምፕ በስልክ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ እና የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በስልክ ተወያዩ።
 
ውይይቱን አስመልክተው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በትዊተር ገፃቸው፥ “ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር የኢትዮ-አሜሪካን ግንኙነት የበለጠ በማጠናከር ዙሪያ አበረታች የስልክ ውይይት አድርገናል” ብለዋል።
 
“የኮቪድ መከላከል እና ቅነሳ ጥረቶች እንዲሁም በበረሃ አንበጣ ቁጥጥር ላይ የሚደረገውን ድጋፍ ለማድነቅ እወዳለሁ” ሲሉም ገልፀዋል።
 
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው በትዊተር ገፃቸው ፥ “ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ተወያይተናል” ብለዋል።
 
“ኢትዮጵያ የህክምና የመተንፈሻ መርጃ (ቬንቲሌተሮች) ያስፈልጓታል” ያሉት ፕሬዚዳንት ትራምፕ፥ “አሜሪካም ድጋፍ ለማድረግ በጥሩ አቋም ላይ ትገኛለች፤ ይህንንም እናደርጋለን” ብለዋል።

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.