Fana: At a Speed of Life!

በሐረሪ የኑሮ ውድነት ጫናን ለማቃለልና በስራ ዕድል ፈጠራ ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል የህዝቡን የኑሮ ውድነት ጫና ለማቃለልና በስራ ዕድል ፈጠራ ላይ በትኩረት እንደሚሰራ የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ ገለጹ፡፡

የሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ በየደረጃው የሚገኙ ከፍተኛ አመራሮች በበጀት ዓመቱ ቀሪ ወራት የህብረተሰቡን ጥያቄዎች ለመመለስ የጋራ ርብርብ በሚደረግባቸው ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ተወያይተዋል።

በብልፅግና ፓርቲ የሐረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ እንደገለፁት ፥ ተቋማት ህብረተሰቡ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች የዕቅዳቸው አካል አድርገው እንዲመልሱ አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል ይደረጋል።

ፓርቲው ለህዝብ የገባውን ቃል በብቃት ለመምራትና በውጤታማነት ለመፈጸም አመራሩ ቀጣይ ዋናው ተልዕኮ የህዝቡን የኑሮ ውድነት ጫናን ለማቃለል የተጀመሩ መልካም ስራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል በትኩረት መስራት አለበት ብለዋል፡፡

በተጨማሪም በወጣቶችና በሴቶች የስራ ዕድል ፈጠራ ተጠቃሚነት ላይ በማተኮር በቁርጠኝነት መስራት እንዳለበትም ነው ያነሱት።

የሥራ ዕድል ፈጠራ ለኢኮኖሚው፣ ለማኅበራዊ፣ ለፖለቲካው ወሣኝ በመሆኑ የአመራሩን ቁልፍ ትኩረት ከሚሹ ዘርፎች አንዱ ነው ያሉት አቶ አብዱጀባር ፥ አመራሩ የዚህን ጥልቀት ተረድቶ መምራት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

ግልፅነት ያለው የስራ ዕድል ፈጠራን በመከተል በቀሪ ወራት የወጣቶችንና የሴቶችን የስራ ዕድል ተጠቃሚነት ጥያቄ ለመመለስ በጋራ መረባረብ እንደሚገባም ነው ያሳሰቡት።

በክልሉ የህዝቡን የኑሮ ውድነት ጫና ለማቃለል ከመቼውም ጊዜ በላቀ በቁርጠኝነት እየሰራን እንገኛለንም ብለዋል ኃላፊው።

በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተሰሩ ስራዎች ውጤቶች እየታዩ ሲሆን ፥ ይህ ስራ በቀጣይም በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥል አንስተዋል።

የተለያዩ ምርቶችን በመደበቅና በመመሳጠር ሰው ሰራሽ የኑሮ ውድነት ለመፍጠር የሚሯሯጡ ስግብግብ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ የመውሰድ ስራ በልዩ ትኩረት እንሚሰራ መግለጻቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.