Fana: At a Speed of Life!

በአሜሪካ የፌደራል መንግስቱን የብድር ጣራ ከፍ እንዲል የሚፈቅደው ሠነድ ጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ የፌደራል መንግስቱን የብድር ጣራ ከፍ እንዲል የሚፈቅደውን ሠነድ የሀገሪቱ ኮንግረስ አጸደቀ፡፡

የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት ሠነዱን ያጸደቀው 314 ለ 117 በሆነ አብላጫ ድምፅ መሆኑን ቢቢሲ አስነብቧል፡፡

ሠነዱ በፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ፊርማ ፀድቆ ስራ ላይ ከመዋሉ በፊት የአሜሪካ ሴኔት ድምፅ መስጠት ይኖርበታል።

እስከ ፈረንጆቹ ሠኔ 5 ቀን ድረስ መንግስት የብድር ጣራውን ይወስናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የሠነዱ መፅደቅ ለአሜሪካ ህዝብና ኢኮኖሚ መልካም ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

ሴኔቱም ሠነዱን በተቻለ ፍጥነት እንዲያጸድቀውና ወደ ስራ እንዲገባም መጠየቃቸውን ቢቢሲ አስነብቧል፡፡

ይህ የፌደራል መንግስቱን የብድር ጣራ ከፍ የሚያደርገው ህግ ባይፀድቅ ኖሮ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ አለመረጋጋትን ከመፍጠር ጀምሮ መንግስት ለሰራተኞቹ የሚከፍለው ደመዎዝ በካዝና አይኖረውም ነበር።

ይህ ከመሆኑ በፊት በኮንግረሱ ያሉት የሪፐብሊካንና ዴሞክራት ፓርቲዎች አባላት ብርቱ ክርክር ሲያደርጉ ሰንብተዋል።

በተለይም ሪፐብሊካኖች ይህ ህግ እንዳይፀድቅ በመከላከል የፕሬዚዳንት ባይደን አስተዳደር እንዲፈፅማቸው የሚፈልጉትን ቅድመ ሁኔታዎች እንዲቀበል ግፊት ለማድረግ አጋጣሚውን ተጠቅመዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.