Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ፣ ጃፓን እና ፊሊፒንስ የጋራ የባህር ሃይል ልምምድ ሊያደርጉ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ፣ ጃፓን እና ፊሊፒንስ በደቡብ ቻይና ባህር የጋራ የባህር ሃይል ልምምድ ሊያደርጉ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

የጋራ የባህር ሃይል ልምምዱ ሶስቱ ሀገራት በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያከናውኑት መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

የጋራ ልምምዱ አሜሪካ በቀጠናው ወታደራዊ ዲፕሎማሲዋን ለማሳደግ እና ስትራቴጂያዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ የምታከናውነው መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከዚህ ባለፈም ልምምዱ ቻይና በደቡብ ቻይና በህር ቀጠና ለምታካሂደው ተደጋጋሚ ወታደራዊ ልምምድ አጸፋዊ ምላሽ መሆኑንም ነው አልጀዚራ በዘገባው ያስነበበው።

ለሰባት ቀናት በሚካሄደው የጋራ የባህር ሃይል ልምምድ አውስትራሊያ በታዛቢነት እንደምትሳተፍ ታውቋል።

በተመሳሳይ ቻይና በደቡብ ቻይና ባህር ቀጠና ከአጋር ሀገራት ጋር የምታደርገው የጋራ ወታደራዊ ልምምድ እየጨመረ መምጣቱ ተጠቁሟል፡፡

በተያዘው የፈረንጆች ዓመት ብቻም ቻይና ከሲንጋፖር ፣ ካምቦዲያ ፣ላኦስ እና ኢንዶኔዢያ ጋር የጋራ ወታደራዊ ልምምድ አድርጋለች፡፡

አሜሪካ እና ቻይና በቀጠናው የሚያደርጉት ወታደራዊ ጨዋታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ መምጣቱ የሀገራቱን ግንኙነት ይበልጥ እንዳያሻክረው ተሰግቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.