Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል 2 ሺህ 160 የውሃ መሳቢያ ፓምፖችን ለመስኖ ልማት ማህበራት አስረከበ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት 2 ሺህ 160 የውሃ መሳቢያ ፓምፖችን ለመስኖ ልማት ማህበራት አስረከበ።

የርክክብ ስነ ስርዓቱ የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በተገኙበት በዛሬው እለት በአዲስ አበባ በሚገኘው የርእሰ መስተዳድሩ ጽህፈት ቤት ቅጥር ግቢ ነው የተካሄደው።

ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በዚሁ ወቅት፥ በክልሉ አርሶ አደሩ ከዝናብ ጠባቂነት ተላቆ በመስኖ ልማት በመታገዝ በዓመት ሶስት ጊዜ እንዲያመርት እየተሰራ ነው ብለዋል።

በዚህም መሰረት ትላለቅ እና አነስተኛ የመስኖ ልማት እና የውሃ መሳቢያ ፓምፖችን በመጠቀም እየተሰራ መሆኑንም አስታውቅዋል።

በአሁኑ ወቅትም በክልሉ በ126 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የመስኖ ልማት ስራ እየተካሄደ መሆኑንም አቶ ሽመልስ አብዲሳ አክለው አንስተዋል።

ብዛታቸው 2 ሺህ 160 የሆነው የውሃ መሳቢያ ፓምፖች በክልሉ ለሚገኙ 21 ዞኖች ነው የተከፋፈሉት።

የውሃ መሳቢያ ፓምፖቹ በሰከንድ 16 ሊትር ውሃን በመሳብ መወርወር የሚችሉ ሲሆን፥ አንዱ ፓምፕም ከ10 እስከ 16 ሄክታር መሬት ማልማት የሚችል መሆኑም ታውቋል።

የክልሉ መንግስት አርሶ አደሩን ከዝናት ጠባቂነት ለማላቀቅ በ15 ቢሊየን ብር የተለያዩ የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶችን እያከናወነ መሆኑም ተነግሯል።

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.