Fana: At a Speed of Life!

ከልማት አጋሮች የሚገኘውን ሃብት በግጭት የተጎዱ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም እንዲውል አሳታፊ አሰራር ተግባራዊ እየተደረገ ነው- ወ/ሮ ሰመሪታ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከልማት አጋሮች የሚገኘውን የውጭ ሃብት በግጭት የተጎዱ ዜጎችን መልሶ በማቋቋምና በሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶች በማዋል አሳታፊ አሰራር ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ሚኒስቴሩ በመሰረታዊ አገልግሎቶች አቅርቦቶች በተከናወኑ ስራዎች ላይ የልማት አጋሮች፣ የፌዴራል፣ የክልልና የከተማ አስተዳደሮችን ያካተተ የጋራ የግምገማ መድረክ አካሂዷል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰመሪታ ሰዋሰው÷ የኢትዮጵያ መንግስት ዓለም ባንክን ጨምሮ ከተለያዩ የልማት አጋሮች በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የጋራ ተጠቃሚነትንና ፍትሃዊ አገልግሎትን ባልተማከለ ደረጃ እየሰጠ ነው ብለዋል፡፡

በዚህም በትምህርት፣ በጤና፣ በውሃ፣ በግብርና እና በገጠር መንገድ መሰረታዊ አገልግሎቶች አሰጣጥን የሚያሳድጉ ሰራዎችን ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል ነው ያሉት።

የመርሐ ግብሩ ትግበራ ሂደት ፍትሃዊ የሆነ የመሠረታዊ አገልግሎት ተጠቃሚነትን በማሻሻል እና በክልሎች ደረጃ ተጠያቂነትን እንዲሰፍን በማደረግ ረገድ ጉልህ ሚና እንደሚገኝም አንስተዋል፡፡

ከልማት አጋሮች የሚገኘውን የውጭ ሃብት በግጭት የተጎዱ ዜጎችን መልሶ በማቋቋምና በሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶች በማዋል አሳታፊ የሆነ አሰራር ተግባራዊ እየተደረገ እንደሆነ መግለጻቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

የመሰረታዊ አገልግሎትን በፍትሃዊነት በሁሉም ክልሎች ለሚገኙ ዜጎች ለማዳረስ መንግስት የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት ወ/ሮ ሰምሪታ ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.