Fana: At a Speed of Life!

ቅዱስ ጊዮርጊስ የፕሪሚየር ሊጉን መሪነት ያጠናከረበት ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 24 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ27ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ሁለተኛ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ለገጣፎ ለገዳዲን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡

በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቶጎዋዊው አጥቂ ኢስማኤል ኦሮ አጎሮ በ16ኛው እና የአማካይ ተጫዋቹ ሀይደር ሸረፋ በ58ኛው ደቂቃ ለፈረሰኞቹ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

አጥቂው ኢብሳ በፍቃዱ በ94ኛው ደቂቃ ለለገጣፎ ለገዳዲ ብቸኛዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ውጤቱንም ተከትሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥቡን ወደ 58 በማሳደግ ከተከታዩ ባህር ዳር ከተማ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ስምንት ከፍ አድርጓል።

በአንጻሩ ቀድሞ ከፕሪሚየር ሊጉ መውረዱን ያረጋገጠው ለገጣፎ ለገዳዲ በ15 ነጥብ 15ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ኢስማኤል ኦሮ አጎሮ በውድድር ዓመቱ ያስቆጠራቸውን ግቦች ወደ 23 ከፍ በማድረግ የከፍተኛ ግብ አግቢነት መሪነቱን አጠናክሯል።

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ27ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ቀትር ላይ በተደረገው ጨዋታ ሲዳማ ቡና እና አርባ ምንጭ ከተማ አንድ አቻ መለያየታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.