3ኛው ዓለምአቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ መካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 3ኛው ዓለምአቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ በቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ መካሄድ ጀምሯል።
ኮንፈረንሱ በአርብቶ አደር እና የአየር ንብረት ለውጥ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ተብሏል።
ዓለምአቀፍ የምርምር ኮንፈረንሱ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ አደጋዎችን መቋቋም በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ምክክር ያደርጋል።
በኮንፈረንሱ ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገራት የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ የዘርፉ ተመራማሪዎችን ጨምሮ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው።
የፓናል ውይይቶች፣ የልምድ ልውውጦችና በዘርፉ የተደረጉ የምርምር ስራዎች በኮንፈረንሱ ይቀርባሉ፡፡
በዙፋን ካሳሁን እና ድንቃ ባጫ
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!