ከዳንግላ-ግልገል በለስ የተገነባው ከፍተኛ የኤሌክትሪክ መስመር አገልግሎት መስጠት ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከዳንግላ እስከ ግልገል በለስ የተገነባው የ66 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኤሌክትሪክ መስመር አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡
መስመሩ ለረጅም ጊዜ አገልግሎት የሰጠ፣ ምሰሶዎቹ ያረጁና የዘመሙ በመሆኑ በተደጋጋሚ ጊዜ የሃይል መቆራረጥ ችግር ሲፈጠር መቆየቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መረጃ ያመላክታል፡፡
ችግሩን ለመቅረፍ 140 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የመልሶ ግንባታ ስራ የተከናወነ ሲሆን ÷ በዚህም ከ650 በላይ ምሰሶዎች መተከላቸው ተጠቁሟል፡፡
የተከናወነው የመልሶ ግንባታ በአካባቢው የሚስተዋለውን የኤሌክትሪክ መቆራረጥ ለመቀነስና አገልግሎቱን አስተማማኝ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታል ተብሏል፡፡
መስመሩ ፓዊ፣ ቻግኒ፣ ግልገል በለስ፣ ማንኩሽ፣ ድባጢ እና ዚገም ከተሞችን የኃይል ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ነው የተገለጸው፡፡