Fana: At a Speed of Life!

የጋምቤላ ክልል የግብርና ዐውደ ርዕይ ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳይንስ ሙዚየሙ የተዘጋጀው የጋምቤላ ክልል የግብርና ዐውደ ርዕይ ተከፈተ፡፡

የጋምቤላ ክልል ከፍተኛ አመራሮች እና የፌደራል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀውን የግብርና ሳይንስ አውደ ርዕይ እየጎበኙ ነው።

ከዚህ ጎን ለጎን በሳይንስ ሙዚየሙ የተዘጋጀውን የጋምቤላ ክልል የግብርና ዐውደ ርዕይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አለሚቱ ኡሙድ ከፍተዋል።

በክልል ደረጃ በተዘጋጀው የግብርና አውደ ርዕይ ላይ በክልሉ የተመረቱ አትክልትና ፍራፍሬ፣ የእንስሳት ተዋጽኦና ሌሎች የግብርና ዘርፍ ሀብቶች ለዕይታ መቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የሚያስችሉ ዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂዎችና ዘርፉን ሊያሳድጉ የሚችሉ ሌሎች የፈጠራ ስራዎችም በአውደ ርዕዩ ተካተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.