Fana: At a Speed of Life!

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የብዝሃነት ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የብዝሃነት ሚኒስትር ሼክ ናሃያን ሙባረክ አል ናሃያን ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ ወቅት÷ ሼክ ናሃያን ሙባረክ አል ናሃያን ቅዱስ ፓትርያርክ ለጉብኝት ወደ አቡዳቢ በመምጣታቸው ክብር እና ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸዋል፡፡

ጉብኝታቸውም በኢትዮጵያና በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች መካከል ያለው የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር አዎንታዊ ሚና እንደሚጫወት አንስተዋል፡፡

ቅዱስነታቸው በበኩላቸው÷ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች መንግስት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ህንፃ መገንቢያ ለሰጠው መሬት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ለተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ሕዝብና መሪዎች መልካም ምኞታቸውን እንደገለጹም በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.