Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ  በተለያዩ ተቋማት የሚተከሉ 800 ሺህ የሚደርሱ ችግኞች መዘጋጀታቸው ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለዘንድሮው አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በአዲስ አበባ በተለያዩ ተቋማት የሚተከሉ 800 ሺህ የሚደርሱ ችግኞችን ማዘጋጀቱን የጉለሌ እጽዋት ማዕከል ገለጸ።

የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ጉተማ ሞረዳ (ዶ/ር) እንደገለጹት÷ በዘንድሮው ዓመት በአዲስ አበባ በተለያዩ ተቋማት የሚተከሉ 800 ሺህ ችግኞች ተዘጋጅተዋል።

ማዕከሉ ለዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አገር በቀል የሆኑ ለአፈርና የውሃ ጥበቃ፣ ለፍራፍሬና ለምግብነት የሚውሉትን ጨምሮ አካባቢን ለማስዋብ የሚውሉ ችግኞችን አፍልቶ ማዘጋጀቱን ጠቁመዋል።

ማዕከሉ ችግኞችን ከማፍላት ጎን ለጎን 705 ሄክታር መሬት ላይ በ2014 ዓ.ም ከተከላቸው ችግኞች ውስጥ 90 በመቶው መጽደቁን መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በአገር አቀፍ ደረጃ ባለፉት አራት ዓመታት በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር 25 ቢሊየን ችግኞች መተከላቸው ይታወሳል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.