የሀገር ውስጥ ዜና

ድሬ ጎዳና ሆስፒታል ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ

By Alemayehu Geremew

June 03, 2023

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ109 ሚሊየን ብር ወጪ በአዳማ የተገነባው የድሬ ጎዳና ሆስፒታል በዛሬው ዕለት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል፡፡

ሆስፒታሉ ዘመናዊ የሕክምና መሣሪያዎች የተሟሉለት ሲሆን፥ በሰው ኃይልም በበርካታ ስፔሻሊስት ሐኪሞች የተደራጀ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የጤና አገልግሎት ተቋሙ ሥራ የተጀመረው መሠረታዊ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ማድረግን ዓላማ በማድረግ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

የጤና አገልግሎትን በሁሉም ቦታ ለሁሉም ለማዳረስ በሚል ከ11 ዓመታት በፊት በክሊኒክነት ሥራውን የጀመረው የጤና ተቋም ነው አሁን ወደ ሆስፒታልነት ያደገው።

በትዕግሥት ብርሃኔ