Fana: At a Speed of Life!

በረከት ደሞዝ የ13ኛው ምዕራፍ የፋና ላምሮት የድምጻውያን ውድድር አሸናፊ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 13ኛው ምዕራፍ የፋና ላምሮት የድምጻውያን ውድድር በበረከት ደሞዝ አሸናፊነት ተጠናቀቀ።

በፋና ላምሮት የባለ ተሰጥኦ ድምጻውያን ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ ለፍጻሜ ተፋላሚዎች የቀረበው የገንዘብ ሽልማት መጠን ለመጀመሪያ ጊዜ 1 ሚሊየን ብር ሆኗል።

በዛሬው የፍጻሜ ውድድርም ሐብታሙ ይሄነው፣ ግርማ ሞገስ፣ በረከት ደሞዝ እና ዘውዱ አበበ በፍጻሜ ውድድሩ ከፍተኛው ሽልማት ለመውሰድ ተወዳድረዋል፡፡

በፋና ቴሌቪዥን፣ ሬዲዮ እና በኦንላይን በቀጥታ ሥርጭት የተላለፈው ውድድሩ፥ ተወዳዳሪዎቹ የሙዚቃ ሥራቸውን በሶስት ዙር አቅርበዋል፡፡

በዚህም በረከት ደሞዝ የ13ኛው ምዕራፍ የፋና ላምሮት የድምጻውያን ውድድርን በአንደኝነት በማጠናቀቅ የ400 ሺህ ብር ተሸላሚ ሆኗል፡፡

አድማጭ ተመልካቾችም በፋና ቴሌቪዥን በዕለቱ የሚገለጸውን የተወዳዳሪዎችን ኮድ በ8222 በመላክ አሸናፊ መሆን ይገባዋል የሚሉትን መርጠዋል፡፡

በዚህም በረከት ደሞዝ የ13ኛው ምዕራፍ የፋና ላምሮት የድምጻውያን ውድድርን በአንደኝነት በማጠናቀቅ የ400 ሺህ ብር አሸናፊ ሆኗል፡፡

በሁለተኛ ደረጃም ሃብታሙ ይኄነው 300 ሺህ ብር ተሸልሟል፡፡

በሦስተኛ ደረጃ አሸናፊ በመሆን ያጠናቀቀው ግርማ ሞገስ ሲሆን ፥ 200 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶለታል፤ ዘውዱ አበበ አራተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ የ100 ሺህ ብር ተሸላሚ ሆኗል፡፡

ሽልማቱን ከድምፃዊ ግርማ ተፈራ ካሳ ጋር በመሆን ያበረከቱት የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አድማሱ ዳምጠው የእኳን ደሥ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸው የዛሬው የፋና ላምሮት መድረክ በሦስት ነገሮች የተለየ እንደሆነ ገልጸው ፥ “ቃላችንን እንደከዚህ ቀደሙ በመጠበቅ ሽልማቱን ወደ 1 ሚሊየን ከፍ ማድረጋችን አንዱ ነው” ብለዋል፡፡

በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ፋና ላምሮት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ የራዲዮ አማራጮች በቀጥታ መተላለፍ መጀመሩ እንደሆነ አንስተዋል።

የድምጻዊ ተፈራ ካሳ ልጅ ግርማ ተፈራ ካሳ በእንግድነት የታደመበት መሆኑ ነው ደግሞ ሰስተኛው የፍፃሜውን ውድድር ልዩ ያደረገ ክስተት መሆኑን በመግለፅ፥ ይህንንም ጥበብ በትውልድ ቅብብሎሽ የመጣ ለመሆኑ ማሳያ ነው ብለዋል።

የፍጻሜ ተፋላሚዎቹም በቀጣይ ማለትም በምዕራፍ 14 እና 15 ለፍፃሜ ከሚቀርቡ ተወዳዳሪዎች ጋር ዳግም በአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ይመለሳሉ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.