ማንቼስተር ሲቲ የእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ማንቼስተር ሲቲ የከተማ ተቀናቃኙን ማንቼስተር ዩናይትድ በማሸነፍ የእንግሊዝ ኤፍ ኤፕ ካፕ ዋንጫን አሸንፏል።
11 ሰዓት ላይ በተካሄደው የማንቹሪያ ደርቢ የፍፃሜ ጨዋታ ማንቼስተር ሲቲ በጀርመናዊዉ አጥቂ ኤልካይ ጎንዶጋን ጎሎች 2 ለ 1 በማሸነፍ ዋንጫውን ከፍ አድርገዋል።
ሦስትዮሽ የዋንጫ ጉዟቸውን የቀጠሉት ስፔናዊው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ከውሃ ሰማያዊዎቹ ጋር ሁለተኛ የእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫቸውን ማንሳት ችለዋል።
ሲትዝኖቹ የውድድር ዓመቱን ሁለተኛ ዋንጫ ካዘናቸው ውስጥ ያስገቡ ሲሆን ፥ ሦስተኛ ዋንጫቸውን ለማገኘት በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ከኢንተርሚላን ጋር ለመፋለም ቀጠሮ ይዘዋል።
በሚኪያስ አየለ
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!