ስፓርት

የኢትዮጵያ ሜዳ ቴኒስ ስፖርተኞች ልዑካን ቡድን ሽኝት ተደረገለት

By Alemayehu Geremew

June 03, 2023

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ሀገራት አስተናጋጅነት በሚዘጋጀው የሜዳ ቴኒስ ውድድር ላይ የሚሳተፉ የኢትዮጵያ ስፖርተኞት ልዑካን ቡድን ሽኝት ተደረገለት።

በኮንጎ ኪኒሻሳ እና በሩዋንዳ አዘጋጅነት በሚደረጉት የሜዳ ቴኒስ ሻምፒዮና እና ዓለምአቀፍ ውድድሮች ላይ የሚሳተፉት የወንዶች እና የሴቶች የስፖርት ልዑካን ቡድን ሽኝት እና የእራት ግብዣ ተደርጎላቸዋል።

የአትሌቲክስ ቡድኑ ከ25 ዓመታት በኋላ ነው በዓለምአቀፉ የሜዳ ቴኒስ ውድድር ላይ የሚሳተፈው።

የኢትዮጵያ ቴኒስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሚካኤል ንጉሴ ÷ አትሌቶቹ ከተሳትፎ ባለፈ ውጤት ይዘው እንዲመለሱ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በሁለቱ ሀገራት የሚደረገው የዓለም ሜዳ ቴኒስ ሻምፒዮና ከነገ ጀምሮ በሩዋንዳ ኪጋሊ እንደሚካሄድ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።