Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባ የብሉምበርግ ብስክሌት መሰረተ ልማት ኢንሽዬቲቭ ሽልማት አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ ከተማ የብሉምበርግ ብስክሌት መሰረተ ልማት ኢንሽዬቲቭ አሸናፊ ከሆኑ አስር የዓለማችን ከተሞች አንዷ ሆናለች።

ከአምስት አህጉራት 275 ተወዳድረው ነው 10 ከተሞች የውድድሩ አሽናፊ የሆኑት።

የብሉምበርግ ኢኒሼቲቭ አሸናፊዎቹ ሃገራት ፤ ኢትዮጲያን ጨምሮ ብራዚል ፣ ህንድ ፣ጣሊያን ፣ አልባኒያ ፣ ኒውዝላንድ ፣ፖርቹጋል ፣ ኮሎምቢያ ፣ ኬንያ ፣ሞዛምቢክ መሆናቸው ታውቋል።

አዲስ አበባ በአፍሪካ ትልቁን የሳይክል ጎዳና ለመገንባት የጀመርቻቸው ስራዎችና ወደፊት ይህን ስኬት ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማሸጋገር ያቀረበችው ፕሮፖዛል አሸናፊ አድርጓታል።

የአየር ንብረት ለውጥ መከላከልንና ለህዝቡ ተጨማሪ የትራንስፖርት አመራጭ ማቅረብን ታሳቢ ባደረገው በዚህ ኢንሺዬቲቭ አዲስ አበባ ከተማ የ400 ሺህ ዶላር ታገኛለች ተብሏል።

አሸናፊዎቹ ከተሞች ከገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ የቴክኒክ ድጋፍ እንደሚሰጣቸው ተገልጿል::

ከተሞቹ ከብሉምበርግ ኢኒሸቲቭ በሚያገኙት ድጋፍ የብስክሌት መጓጓዣ ጎዳናዎች በመገንባት ለነዋሪዎች ጤና እና ደህንነት ለማጠናከር እንዲሁም ለዘላቂ ትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚውል መገለጹን ከከተማዋ ከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.