Fana: At a Speed of Life!

ኮርፖሬሽኑ ከጅቡቲው ዳዋሌህ ኮንስትራክሽን ጋር  በጋራ ለመስራት ተስማማ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን እና የጅቡቲው ዳዋሌህ ኮንስትራክሽን ያላቸውን የጋራ ትብብር የሚያጠናክር የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል ፡፡

የአጋርነት ስምምነቱ በኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ እና ሌሎች የመካከለኛው እና የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ዘርፍ  ትብብር መፍጠር የሚያስችል ስለመሆኑ ነው የተገለፀው፡፡

ስምምነቱን  በጂቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ  ዮናስ አያሌው(ኢ/ር) ተገኝተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ጅቡቲ በምትገነባው የሞሉድ ፣ደኺል፣ጋላሞ የ35 ኪሎ ሜትር የመንገድ ፕሮጅክትን ሃላፊነት ወስዶ እየሰራ እንደሚገኝ ከጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.