Fana: At a Speed of Life!

በቻይና ዉሃን በሆስፒታል የነበሩ ሁሉም የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች አገግመው ከሆስፒታል ወጡ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 18፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮሮና ቫይረስ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየባት የቻይናዋ ግዛት የሆነችው ዉሃን ሁሉም የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች አገግመው ከሆስፒታል ወጥተዋል።

የሃገሪቱ የጤና ኮሚሽን ቃል አቀባይ ሚ ፈንግ በዛሬው ዕለት በሆስፒታሉ የቀረ የኮሮና ቫይረስ ታማሚ እንደሌለ ነው የተናገሩት።

ቃል አቀባዩ በፅኑ ህመም ላይ የነበሩት የመጨረሻው ታማሚ ከበሽታው ድነው አርብ እለት ከሆስፒታል መውጣታቸውን ለጋዜጠኞች አስታውቀዋል።

በዚህም ወረርሽኙን ለመከላከል ያልተቋረጠ ትጋት ላደረጉት በመላው ሃገሪቱ የሚገኙ የህክምና ባለሙያዎችን አመስግነዋል።

ምንጭ፦ ሲጂቲኤን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.