Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ባህርዳር ከነማ መቻልን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ27ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ባህርዳር ከነማ መቻልን 3 ለ 2 በማሸነፍ የዋንጫ ተፎካካሪነቱን አጠናክሯል፡፡

ቀን 10 ሰዓት ላይ በተከናወነው  መርሃ ግብር ሀብታሙ ታደሰ ሁለት ጎሎችን ለባህርዳር ከነማ ሲያስቆጥር የምንትስኖት አዳነ ቀሪዋን አንድ ጎል በራሱ መረብ ላይ አሳርፏል፡፡

በረከት ደስታ እና ምንይሉ ወንድሙ ደግሞ የመቻልን ሁለት ጎሎች ያስቆጠሩ  ተጫዋቾች ናቸው፡፡

ውጤቱን ተክትሎ ባህርዳር ከነማ ነጥቡን 53 ያደረሰ ሲሆን÷ በሊጉ ያለውን የዋንጫ ተፎካካሪነትም አስጠብቋል፡፡

መቻል በአንፃሩ በ34 ነጥብ ባለበት 11ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

7 ሰዓት በተከናወነ ሌላኛ መርሃ ግብር ሀድያ ሆሳዕና መውረዱን ያረጋገጠውን ኢትዮ ኤሌክትሪክን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡

ባየ ገዛኸኝ የሀድያ ሆሳዕናን ሁለት ጎሎች  ሲያስቆጥር የኢትዮ ኤሌክትሪክን ብቸኛ ጎል ቃል አብ ውብሸት በራሱ መረብ አስቆጥሯል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.