የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የአንድነት ፓርክ የዕጽዋት ማዕከልን መርቀው ከፈቱ

By Mekoya Hailemariam

June 04, 2023

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአንድነት ፓርክ የዕጽዋት ማዕከልን፣ የአንድነት ቤተ መዛግብትን እና የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የሕክምና ማዕከልን መርቀው ከፈቱ።

የማዕከላቱን መመረቅ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው በኩል የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፥ የዕጽዋት ማዕከሉ ጥቅም ላይ ውሎ በማያውቅ ቦታ ላይ የተሠራ መሆኑን አስታውቀዋል።

ለአንድነት ቤተ መዛግብት እና ለሕክምና ማዕከሉ ደግሞ ሰፋፊ የማዘመን ሥራዎችን በማከናወን ደረጃቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ መደረጉን ነው ያመለከቱት።

አያይዘውም ቦታን በበቂ እና ውጤታማ በሆነ መንገድ መጠቀም እሴት ለመፍጠር አስፈላጊ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።