Fana: At a Speed of Life!

በኮንስትራክሽን ዘርፉ ብቃት ያለው ሀገር በቀል የሰው ሃይል መገንባት የሚያስችል ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለማድረግ እና ብቃት ያለው ሀገር በቀል የሰው ሃይል መገንባት የሚያስችል ውይይት እየተካሄደ ነው።

የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ በሚኒስቴሩ የመሰረተ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወንድሙ ሴታ (ኢ/ ር) እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡

የውይይት መድረኩ የኮንስትራክሽን ዘርፉን ግብዓቶች በሀገር ውስጥ ምርት የመተካት እና ተወዳዳሪነትን ለማሳለጥ የተመቻቸ የፋይናንስ እንዲሁም የመሳሪያዎች አቅርቦት እንዲኖር ለማስቻል ያለመ ነው ተብሏል፡፡

የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ወንድሙ ሴታ (ኢ/ ር) እንዳሉት ÷ ዘርፍ በኢትዮጵያ ሀገራዊ የልማት ፍላጎት ዕድገት ላይ የራሱን አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ የሚገኝ ቢሆንም በውስብስብ ችግሮች እየተፈተነ ይገኛል።

ያሉበትን ውስብስብ ችግሮች በመፍታት ለሚጠበቀው ውጤት እንዲበቃ ለማድረግ ችግሩ በአንድ ተቋም ጥረት ብቻ የሚፈታ እንዳልሆነም አስረድተዋል።

ለዚህም በዘርፉ ባለድርሻ አካላት፣ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የሙያ ማህበራት፣ የግንባታ ዕቃ አቅራቢና አምራቾች የፋይናንስ እና የግብይት ተቋማት ትብብር እና ቅንጅት ያስፈልጋል ብለዋል።

በመድረኩ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሑፎች እየቀረቡ ሲሆን÷ በዋናነት የኮንስትራክሽን ዘርፉ ማደግ ለምን ተሳነው? በሚል ሃሳብ ላይ ሰፊ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በምንይችል አዘዘው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.