Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፉ የነዳጅ ዋጋ ማሻቀቡ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ መሸጫ ዋጋ ማሻቀቡ ተገልጿል፡፡

የነዳጅ ዋጋ ያሻቀበውም ሳዑዲ አረቢያ ከፈረንጆቹ ሐምሌ ወር ጀምሮ ከነዳጅ ወጪንግዷላይ በቀን 1ሚሊየን በርሜል ለመቀነስ ማሰቧን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡

በሳዑዲ አረቢያ ዕቅድ ላይ ነባሮቹ እና በሒደት ቡድኑን የተቀላቀሉት የነዳጅ አምራች እና ላኪ ሀገራት ድርጅት (ኦፔክ) መስማማታቸው ተገልጿል፡፡

ሀገራቱ የነዳጅ ዋጋ ወድቋል በሚል ሰበብም ከ2024 ጀምሮ ከወጪንግዳቸው ላይ በቀን የ1 ነጥብ 4 ሚሊየን በርሜል ነዳጅ ምርት ሊቀንሱ ማሰባቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በእስያ የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በ2 ነጥብ 4 በመቶ ጭማሬ ያሳየ ሲሆን ÷ በበርሜል 77 ዶላር እየተሸጠ መሆኑ በዘገባው ተመላክቷል፡፡

ሳዑዲ አረቢያ ÷ የድፍድፍ ነዳጅ መሸጫ ዋጋ በበርሚል ከ80 ዶላር በላይ ሆኖ መቀጠል አለበት የሚል አቋም እንዳላትም ተጠቅሷል፡፡

የነዳጅ አምራች እና ላኪ ሀገራቱ ከ40 በመቶ በላይ የሚሆነውን የዓለማችንን ድፍድፍ ነዳጅ እንደመቆጣጠራቸው ሥምምነታቸው በዓለም የነዳጅ ወጪ ንግድ ገበያ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር ተጠቁሟል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.