Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል 1 ሺህ 131 ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች ተገኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ከ17ሺህ በላይ የትምህርት ማስረጃዎች ላይ በተደረገ የማጣራት ስራ 1 ሺህ 131 ማስረጃዎች ሀሰተኛ ሆነው መገኘታቸው ተገልጿል፡፡

የደቡብ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የ2015 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም ላይ ትኩረት ያደረገ የምክክር መድረክ እየተካሔደ ነው ፡፡

የቢሮው ኃላፊ አቶ ዘይኔ ቢልካ እንደገለጹት ÷በበጀት ዓመቱ ከ17ሺህ በላይ የትምህርት ማስረጃዎች ላይ በተደረገ የማጣራት ስራ 1 ሺህ 131 የትምህርት ማስረጃዎች ሀሰተኛ ሆነው ተገኝተዋል፡፡

በተጨማሪም÷በክልሉ 5 ሺህ 672 የብቃት ማረጋገጫ ላይ በተደረገ ፍተሻ 767 የብቃት ማረጋገጫዎች ሀሰተኛ ናቸው ብለዋል።

በተቋማት ከ23 ሺህ በላይ መዝገቦች ላይ ፍተሻ ማድረግ መቻሉን የገለጹት አቶ ዘይኔ  ከ4 ሺህ በላይ ቅጥር፣ዝውውር እና የደረጃ እድገት በህገ ወጥ መልኩ መፈጸሙንም ነው የገለጹት፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘም በክልሉ ከ2 ሺህ በላይ አመራሮች እና ባለሙያዎችን ተጠያቂ ማድረግ መቻሉን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.