Fana: At a Speed of Life!

በእርግዝና ወቅት የሚመከሩ የፍራፍሬ አይነቶች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በእርግዝና ወቅት ለጽንስ ለተሟላና አስተማማኝ እድገትና ብስለት እንዲሁም ጥንካሬና አቅም የተመጣጠነ አመጋገብ ይመከራል።

ከዚህ ውስጥ ደግሞ ፍራፍሬን በዚህ ወቅት መመገብ ጠቃሚ መሆኑን ባለሙያዎች ይገልጻሉ።

ቫይታሚን፣ የተለያዩ ንጥረ ነገሮችን፣ ማዕድናትን፣ ፋይበር፣ ፈሳሽ፣ ሃይል ሰጭ ወዘተ በፍራፍሬ ውስጥ ይገኛል።

ፍራፍሬ በተለያየ ሰዓት፣ በስናክ፣ በመክሰስ፣ ከምግብ በኋላ፣ ሌሊት ላይ ፣ በጠዋት ፣ መኝታ ሰዓት ወዘተ ይወሰዳል።

ብርቱካን፣ ሙዝ ፣ አቮካዶ፣ ሎሚ፣ ማንጎ፣ አፕል፣ ሀባብ፣ እንጆሪ፣ ሸክኒት፣ አፕሪኮት፣ የወይን ፍሬ፣ መንደሪን፣ ዘይቱን፣ ቴምር፣ ኮክ፣ የበለስ ፍሬ፣ የሮማን ፍሬ፣ ሆጲ ፍሬ፣ ሊቺ ፍሬ፣ ፕለም ፍሬ፣ ኩዊንስ ፍሬ ፣ ኪዊ ፍሬ፣ ኮኮነት፣ ፐርስሞንስ፣ ኔክታሪን እና የባህር ሎሚ በእርግዝና ወራት የሚመረጡ የፍራፍሬ ዘር ናቸው።

እነዚህን ማግኘት በተቻለና አቅም በፈቀደ ሁኔታ መጠቀም አስተማማኝ ለሆነ የጽንስ አድገት እንደሚጠቅም የህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ።

ይሁን እንጅ የተጠቀሱትን ሁሉ መውሰድ የግድ ሳይሆን አቅም በፈቀደ መጠን ከእነዚህ የሚገኙትን በአማራጭነት መጠቀም እንደሚቻልም ነው የሚገልጹት።

ፍራፍሬ በእርግዝና ወቅት የሚከሩት የፎሊክ አሲድ (folate) መገኛ ናቸው፣ የእርግዝናን የድርቀት ችግር ይቀንሳሉ፣ የጽንስ ሴሎችን ከመጎዳት ለመከላከል፣ ጠዋት ለሚከሰት ችግር፣ ለምግብ መፈጨት፣ ለአይንና አንጎል መጎልበት፣ ለሆድና እግር ቁርጠት እና ቁርጥማትን ለመከላከል፣ ግፊትን ለመከላከል፣ ክብደትን ለመቆጣጠር፣ የጨጓራ ህመምን ለመቀነስ፣ ያለጊዜ ምጥ እንዳይመጣና ሌሎችም በርካታ ጠቀሜታ አላቸው፡፡

ከላይ የተጠቀሱት የፍራፍሬ አይነቶች በመመገብም በእግርዝና ወቅት ጤንነትን መጠበቅ እንደሚቻል ኸልዝ ላይን እና የሜዲካል ኒውስ ቱደይ መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.