Fana: At a Speed of Life!

ፅንፈኝነትንና አክራሪነትን በመከላከል አንድነታችንን ማፅናት ይገባናል – አቶ አብዱጀባር መሀመድ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፅንፈኝነትንና አክራሪነትን በመከላከል አንድነት እና ሠላምን ማጽናት እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ ተናገሩ።

የሐረሪ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ፣ በክልላዊና ሀገራዊ የፀጥታ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂደዋል።

በመድረኩ ላይ በብልፅግና ፓርቲ የሐረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ ውይይቱ  ሀገራዊ እና ክልላዊ የጸጥታ ሁኔታን በሚመለከት የጋራ ግንዛቤ የተያዘበት ነው ብለዋል።

የውይይት መድረኩ በክልሉ ሰላምን ለማጠናከር እና ለዘላቂ ልማትና ብልጽግና ለማረጋገጥ በጋራ መቆም የሚያስችል ግንዛቤ የተያዘበት መሆኑንም አመላክተዋል፡፡

ፅንፈኝነትንና አክራሪነትን በመከላከል አንድነት እና ሰላምን ማጽናት ይገባል ያሉት ሀላፊው በዚህም አመራሩ የመሪነት ሚናውን በአግባቡ እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

መላው የክልሉ ህዝብም እየታየ የሚገኘው አንፃራዊ ሰላም እንዲጎለብት የተለመደ ድጋፉን እንዲያጠናክር መጠየቃቸውን ከሐረሪ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.