የሀገር ውስጥ ዜና

የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አሥፈፃሚ ኮሚቴ 2 አዳዲስ አባላትን አካተተ

By Alemayehu Geremew

June 05, 2023

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አሥፈፃሚ ኮሚቴ ሁለት አዳዲስ አባላትን በኮሚቴው ውስጥ አካትቷል።

ፓርቲው በተለያዩ ምክንያቶች በተጓደሉ የሥራ አሥፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ምትክ ነው አዳዲስ አመራሮችን በኮሚቴው አባልነት የመደበው፡፡

በዚህ መሠረትም አቶ አብዱ ሁሴን እና አቶ ይርጋ ሲሳይ ኮሚቴውን በአባልነት መቀላቀላቸውን የፓርቲው መረጃ ያመላክታል።

አመራሮቹ የረጅም ዓመት የፖለቲካ ልምድ ያካበቱ እና ፓርቲው የጀመረውን ሀገራዊና አካታች የብልጽግና ጉዞ እንደሚያግዙ መታመኑ ተጠቁማል፡፡