Fana: At a Speed of Life!

በሱዳን ተፋላሚ ሃይሎች መካከል በቀጠለው ግጭት በካርቱም ዘረፋ እና ተኩስ መባባሱ ተሰማ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 28 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች መካከል በቀጠለው ግጭት በመዲናዋ ካርቱም ዘረፋ እና ተኩስ ተባብሶ መቀጠሉ ተነግሯል፡፡

በተፋላሚ ሃይሎች መካከል ተደርሶ የነበረው ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት መጠናቀቁን ተከትሎም ግጭቱ በካርቱም ምዕራባዊ አቅጣጫ ይበልጥ ማገርሸቱን ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

በአንጻሩ የአሜሪካ እና ሳዑዲ ዓረቢያ መንግስታት ተፋላሚ ሃይሎቹ አዲስ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደርሱ እና ስምምነቱን ገቢራዊ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡

ተባብሶ በቀጠለው የሱዳን ግጭት 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸው ሲፈናቀሉ፥ 400 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ወደ ጎረቤት ሀገራት መሰደዳቸውን ቲ አር ቲ ዘግቧል፡፡

በግጭቱ ዋና ከተማዋ ካርቱምከፍተኛ ውድመት እያስተናገደች ሲሆን፥ ዝርፊያ እና ስርዓት አልበኝነት ተጠናክሮ መቀጠሉም ተነግሯል፡፡

ይህን ተከትሎም ዜጎች በጤና ጣቢያዎች እና ሌሎች መሰረተ ልማቶች ላይ አገልግሎት ለማግኘት መቸገራቸው ነው የተገለጸው፡፡

በሌላ በኩል በሰሜን ዳርፉር ግዛት እንደ አዲስ በተቀሰቀሰው ግጭትም የማህበረሰብ አንቂዎችን ጨምሮ ከ40 በላይ ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.