Fana: At a Speed of Life!

የግል ፋይናንስ ተቋማትን ለማነቃቃት ያለመ ፎረም ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) “ድብልቅ ፋይናንስን” ተግባራዊ ለማድረግ እና የግል ፋይናንስ ተቋማትን ማነቃቃት የሚያስችል ፎረም በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡

የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው÷ፎረሙ በኢትዮጵያ የግሉን ዘርፍ በማሳተፍ እና ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት ሚና እንደሚኖረው ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ከተለመዱት የፋይናንስ ምንጮች በተጨማሪ ከተለያዩ አማራጮች ገቢ ለማሰባሰብ የሚያስችል እርምጃ እየወሰደ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

“የድብልቅ ፋይናንስ” ስርዓት በአግባቡ ከተተገበረ ከፍተኛ የልማት አቅም መፍጠር የሚያስችል መሆኑን ነው የገለፁት፡፡

መንግስት ባደረገው የሀገር ውስጥ የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ የንግድ ስርዓቱን በማሻሻል በርካታ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ መቻሉን ወ/ሮ ሰመሪታ አስረድተዋል፡፡

በኢትዮጵያ የሚደረገውን የተቀናጀ የፋይናንስ ፍሰት ለማሳደግ መንግስት ቁርጠኛ ነው ማለታቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.