Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች የዊንዶው ኦፍ አፍሪካ ፓርክ ግንባታ ስራን አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የዊንዶው ኦፍ አፍሪካ ፓርክ ግንባታ ስራን በዛሬው ዕለት አስጀምረዋል፡፡
 
የዊንዶው ኦፍ አፍሪካ ፓርክ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አጠገብ ቀደም ብሎ ለፓርክነት ተከልሎ በነበረ ስፍራ ላይ የሚገነባው ሲሆን ÷ አጠቃላይ 84 ሄክታር መሬት እንደሚሸፍን ተመላክቷል።
 
በፕሮጀክቱ የእያንዳንዱን የአፍሪካ ሀገር ባህል፣ወግ እና ማንነት የሚያንጸባርቁ ቅርሶች እንደሚቀመጡም ነው የተገለጸው።
 
ከንቲባ አዳነአቤቤ በማስጀመሪያ ስነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ በለውጡ ማግስት ከገባነው ቃል አንዱ አዲስ አበባን እንደስሟ ውብና አዲስ እናረጋታለን የሚል ነበር፤ ያንንም በተግባር እያረጋገጥን ነው ብለዋል፡፡
 
የአፍሪካ መዲና ወደ ሆነችው አዲስ አበባ የአፍሪካ ወንድሞቻችን ሲመጡ ራሳቸውንና መልካቸውን የሚመለከቱበት ትልቅ ፕሮጀክት ነው ያስጀመርነውም ብለዋል።
 
በመጀመሪያው ምዕራፍ በ14 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ የስፖርት ማዘውተሪያ፣ የመዝናኛ ፣ የመናፈሻ ፣ የአረንጓዴ ስፍራዎች፣ ሰው ሰራሽ ሃይቅ እና መዋኛ ገንዳዎች፣የተሽከርካሪ ማቆሚያዎችን እንዲሁም የህጻናት መጫዎቻ ስፍራዎችን በውስጡ እንደሚይዝ ተጠቁሟል፡፡
 
በዓለምሰገድ አሳዬ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.