200 የኩባ ሐኪሞች የኮሮና ቫይረስን ለመዋጋት ወደ ደቡብ አፍሪካ ሊያቀኑ ነው
አዲስ አበባ፣ሚያዚያ 18፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) ደቡብ አፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመዋጋት የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ 200 የሚሆኑ የኩባ ሀኪሞች ወደ ሀገሪቱ ሊያቀኑ መሆኑ ተሰምቷል።
ዶክተሮቹ ደቡብ አፍሪካ ከደረሱ በኋላም በሀገሪቱ ወደ ሚገኙ የተለያዩ ክልሎች እንደሚሰማሩም ነው የተነገረው።
ሀኪሞቹ ኮቪድ -19ን ለመዋጋት ኩባን እርዳታ ለጠየቁ 22 አገሮች ከተላኩ 1 ሺህ 200የጤና እንክብካቤ ሠራተኞች ውስጥ የሚካተቱ ናቸውም ነው የተባለው፡፡
ደቡብ አፍሪካ ወረርሽኙን ለመከላከል በመላው ሀገሪቱ ጥላው የነበረውን ጥብቅ የእንቅስቃሴ ገደብ ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ ማላላት እንደምትጀምር ተገልጿል፡፡
በዚህም ከ 1ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ወደ ሥራ እንዲመለሱ የሚፈቀድላቸው ይሆናል ተብሏል።
ከዚያም ባለፈ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች እንደገና የሚከፈቱ ሲሆን ትኩስ የምግብ አቅርቦት እና ሲጋራዎች እንዲሸጡ ይፈቀዳል ነው የተባለው፡፡
ነገር ግን የአልኮል ሽያጭና እና የሕዝብ ስብሰባዎች እንደታገዱ እንደሚቆዩ ተነግሯል።
በደቡብ አፍሪካ እስካሁን በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ 4 ሺህ 361 ሰዎችን የተያዙ ሲሆን 86 የሚሆኑትን ደግሞ ለህልፈት ዳርጓል።
ምንጭ፡-ቢ.ቢ.ሲ