Fana: At a Speed of Life!

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የፌደራል መንግስት የ2016 ረቂቅ በጀት 801 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር እንዲሆን ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 21ኛ መደበኛ ስብሰባ የ2016 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት ረቂቅ የበጀት አዋጅ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

የፌዴራል መንግስት የ2016 በጀት በአስር ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ የተቀመጡ ግቦችን ታሳቢ በማድረግ፣ የሀገር ደህንነት ከማስጠበቅ፣ በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ ችግሮች ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጐችን ከመርዳት፣ በህግ ማስከበር ዘመቻው የወደሙ መሰረተ ልማቶች መልሶ ከማቋቋም፣ በቀጣይ ሊኖር የሚችለውን የማህበራዊና የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን አቅጣጫዎችና ዓላማዎች ከማሳካት አኳያ የተቃኘ ሲሆን የ2016 – 2020 የመካከለኛ ዘመን የማክሮ ኢኮኖሚ እና የፊሲካል ማዕቀፍን መሠረት በማድረግ ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው፡፡

በዚሁ መሰረት ለፌደራል መንግስት መደበኛ ወጪዎች ብር 369 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር፣ ለካፒታል ወጪዎች ብር 203 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር፣ ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ ብር 214 ነጥብ 07 ቢሊየን ብር፣ ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ 14 ቢሊየን ብር በጠቅላላው 801 ነጥብ 65 ቢሊየን ብር ሆኖ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡

ምክር ቤቱም በቀረበው የፌዴራል መንግሥት የ2016 በጀት ረቂቅ አዋጅ ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.