Fana: At a Speed of Life!

በኬርሰን የሚገኘው የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ በከፊል መውደሙ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 29 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬርሰን ከተማ በድኔፕር ወንዝ ላይ የሚገኘው የካኮቭስካያ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ዛሬ ማለዳ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት የከተማው ከንቲባ ተናግረዋል፡፡

የኖቫያ ካኮቭካ ከንቲባ ቭላድሚር ሊዮንቴቭ ለሪያ ኖቮስቲ እንደገለፁት÷ የግድቡ የላይኛው ቁልፍ የመሠረተ ልማት ክፍል በአካባቢው በተሰነዘረ ጥቃት ወድሟል ብለዋል።

የግድቡ የጎርፍ ማስገቢያ በሮች ላይ ጉዳት በመድረሱ ውሀው ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ እንደፈሰሰ እና የየታችኛው የግደቡ መዋቅር ለጊዜው ጥቃቱን መቋቋም መቻሉንም ነው የተናገሩት።

ክስተቱን ትልቅ “የአሸባሪነት ተግባር” ሲሉ የገለፁት ሊዮንቴቭ የታችኛው የውሃ መጠን እስከ 2 ነጥብ 5 ሜትር ከፍ ማለቱን ጠቅሰው፥ አሁን ላይ አካባቢውን አስለቅቆ የሚያስኬድ ነገር እንደሌለ ገልፀዋል።

ቀደም ሲል የጣለው ከፍተኛ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ የውሃው መጠን መጨመሩን በመጠቆም÷ የከፋ ችግር ሊከሰት የሚችል ከሆነ የአካባቢው ባለስልጣናት ለዜጎች እርዳታ ለመስጠት ዝግጅት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል፡፡

በከተማ ውስጥ የሚሰጡ ሁሉም አገልግሎቶች እና ሁሉም የአስተዳደር ሰራተኞች በተጠንቀቅ እንደሚገኙ የገለፁት ከንቲባው÷ ኤሌክትሪክ፣ ጋዝ፣ ኢንተርኔት እና የመገናኛ ዘዴዎች ለተጠቃሚ ክፍት ናቸው ማለታቸውን አር ቲ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.