Fana: At a Speed of Life!

በሰበታ ከተማ ለ1 ሺህ 70 አባወራዎች  ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኡስታዝ አቡበከር አህመድ  የረመዳን ጾም  እና የኮቪድ 19 ወረርሽኝን በማስመልከት በሰበታ ከተማ ላሉ ከሶማሌ ክልል ለተፈናቀሉ 1 ሺህ 70 አባወራዎች ድጋፍ አደረጉ።

ኡስታዝ አቡበከር ከአንድ ቱርካዊ ባለሀብት ጋር በመተባበር በሰበታ ለሚገኙ  ከቀያቸው ለተፈናቀሉ  ሁሉም አባወራዎች ድጋፉን አበርክተዋል።

በዚህም ድጋፍ 10ኪሎ ዱቄት፣ 10ኪሎ መኮሮኒ፣ 5ኪሎ የሾርባ እህል፣ 3ሊትር ዘይት እና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች  መለገሳቸው ነው የተገለጸው።

የድጋፍ አስተባባሪ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ  ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት፥ ድጋፉ ከሶማሌ ክልል ተፈናቅለው በሰበታ ከተማ ለሚኖሩት 1070 አባወራዎች ከአምስት ሺህ በላይ ለሚሆኑ ቤተሰቦች መደረጉን ተናግረዋል፡፡

አያይዘውም ወቅቱ  የረመዳን ጾም በመሆኑና በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ዜጎች ከቤታቸው ባለመውጣታቸው የእለት ገቢያቸው ዝቅተኛ የሆኑ  የህብረተሰብ ክፍሎች ችግር እንዳያጋጥማቸው የተደረገ ነው ብለዋል።

ከዚያም ባለፈ መንግስት የቫይረሱን ስረጭት ለመግታት የሚያደረገውን ጥረት ለመደገፍ  ያለመ መሆኑን  ኡስታዝ አቡበከር ተናግረዋል፡፡

አክለውም በረመዳን ወር የሚደረግ ሰደቃ ከሌላው ጊዜ የበለጠ አጅር ያለው መሆኑን እና የአላህን እዝነት ለማግኘት እንዲህ መተዛዘን እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

አሁን ላይ የተደረገው ድጋፍ 1 ሚሊየን 300 ሺህ ብር  ግምት ያለው መሆኑንም በመጠቆም ፥ መሰል ድጋፎችን በጋራ በማድረግ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች በዚህ አስቸገሪ ወቅት ልንደርስላቸው ይገባልም ነው ያሉት ።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.