Fana: At a Speed of Life!

ሠላምና አንድነትን ለማጠናከር የሃይማኖት አባቶችን ሚና ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሠላምና አንድነትን በማጠናከር ረገድ የሃይማኖት አባቶችን ሚና ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

የብልጽግና ፓርቲ የሐረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽኅፈት ቤት የሥራ ኃላፊዎች ÷ በክልሉ ከተለያዩ ወረዳዎች ከተውጣጡ የሃይማኖት አባቶች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር አካሂደዋል።

በውይይቱም የብልጽግና ፓርቲ የሐረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽኅፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አብዱጀባር መሐመድ ÷ ሐረር የሠላም፣ የመቻቻልና የአብሮነት ከተማ መሆኗን ገልጸዋል።

አያይዘውም ይህን መልካም እሴት ማጠናከር ይገባል ማለታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ሠላምና አንድነት ከማጠናከር አንፃር በተለይ የሃይማኖት አባቶች የሚያበረክቱት አስተዋጽዖ የጎላ መሆኑን ጠቁመው ÷ በየዕምነት ተቋማቸው ስለ ሠላምና አንድነት በማስተማር ኃላፊነታቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።

የክልሉ ሠላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥላሁን ዋደራ በበኩላቸው ÷ አሁን በክልሉ እየታየ ያለውን አንጻራዊ ሠላም ለማስቀጠል ሁሉም በጋራ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

የሃይማኖት አባቶችም ለሠላም ዘብ በመቆም ሃይማኖታዊ ኃላፊነታቸውን መወጣት እንደሚገባቸው አስታውሰዋል።

በውይይቱ ላይ የተገኙ የሃይማኖት አባቶች ÷ የክልሉን ሠላምና የሕዝቦች አብሮ የመኖር ዕሴት እንዲጠናከር ሚናቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.