የአፍሪካ ዞን 4 የጎልፍ ስፖርት ሻምፒዮና ውድድር የመክፈቻ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ዞን አራት የጎልፍ ስፖርት ሻምፒዮና ውድድር የመክፈቻ መርሐ ግብር ጦር ኃይሎች በሚገኘው ጎልፍ ክለብ እየተካሄደ ነው፡፡
በመክፈቻ መርሀ ግብሩ የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ ቀጄላ መርዳሳን ጨምሮ የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንዲሁም የጎልፍ ስፖርት ቤተሰቦች ተገኝተዋል።
ውድድሩ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ከግንቦት 29 እስከ ሰኔ 4 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚካሄድም ተገልጿል፡፡
በአፍሪካ ዞን አራት የጎልፍ ስፖርት ሻምፒዮና ውድድር ላይ ለመሳተፍ እስካሁን አምስት ሀገራት አዲስ አበባ እንደገቡ የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።